ሻላ ሐይቅ

Ethiopia / Oromia / Negele /
 ሐይቅ, caldera (en)

የሻላ ሐይቅ በጥልቀት፣ እንዲሁም በውኃ ይዘት መጠን አንፃር ሲታይ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሐይቆች ሁሉ በመብለጥ የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል። ሐይቁ በዋናው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ፣ ከባሕር ጠለል 1,559 ሜትር (5,115 ጫማ) ከፍታ ላይ፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል፣ በሞያሌ መንገድ 225 ኪሎ ሜትር (140 ማይል) ርቀት ላይ ይገኛል።

የሐይቁ ርዝመት 27ኪሜ (17 ማይል)፣ ስፋት 16ኪሜ (10 ማይል)፣ አጠቃላይ ስፋት (የቆዳ ስፋት) 314 ኪሜ² (121 ማይል²) ነው። የሻላ ሐይቅ ከፍተኛ ጥልቀት 266 ሜትር (873 ጫማ)፣ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ጥልቀት 86 ሜትር (282 ጫማ) ነው። ሐይቁ የሚይዘው የውኃ መጠን 38 ቢሊየን ሜትር³ (1.34 ትሪሊየን ጫማ³) እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን፣ ይህ የውኃ መጠን በሌሎቹ የኢትዮጵያ አራት ሐይቆች፣ ማለትም፣ ጣና፣ ዝዋይ፣ አብያታ፣ ላንጋኖ እና የአዋሳ ሐይቆች በአንድ ላይ ሆነው ከሚይዙት የውኃ መጠን እጅግ የላቀ ነው።

ሻላና አብያታ ሐይቆች፣ በአብያታ-ሻላ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የተካለሉ መሆናቸው ቢታወቅም፣ ይህ ብሔራዊ ፓርክ፣ ያለ አግባብ በሰው ልጅ ሊፋረሱ እና ሊደመሰሱ ከበቁት የሀገሪቱ ብሔራዊ ፓርኮች ውስጥ አንዱ ለመሆኑ አከራካሪ አይደለም። ደምቆና አምሮ ይታይ የነበረው ያሁሉ የግራር ዛፍ ተጨፍጭፎ በምትኩ ከፓርኩ ክልል ውስጥ የሚታየው፣ የግለሰቦች መኖሪያ ቤትና እርሻ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የአብያታ ሐይቅ የውኃ መጠን ማሽቆልቆል፣ ከማሳዘን አልፎ፣ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሷል። አንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀና ተደማጭነት ያለው የትራቭል ጋይድ መጽሄት፣ ስለ አብያታ-ሻላ ብሔራዊ ፓርክ በአጭሩና በትክክል እንዳስቀመጠው፣ አብያታ-ሻላን የተጠበቀ ፓርክ ነው ማለት እንደማፌዝ ያህል ነው ብሎታል። እዚህ ላይ ቁምነገሩ ማን አደረገው ወይም መች ነው የተደረገው የሚለው ሳይሆን፣ አሁን ምን መደረግ ይኖርበታል የሚለው ነው።
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   7°27'54"N   38°30'41"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ13 ዓመታት በፊት