ዓባያ ሐይቅ

Ethiopia / Southern / Chencha /

የዓባያ ሐይቅ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኝ፣ በርዝመት በሀገሪቱ ውስጥ የመጀመሪያውን ቦታ፣ በትልቅነት ደግሞ ከጣና ሐይቅ ቀጥሎ ሁለተኛውን ቦታ ይይዛል።

ለሐይቁ ዋና ገባር የሆነው የብላቴ ወንዝ በስተሰሜን በኩል ከሐይቁ ይቀላቀላል። የዓባያ ሐይቅ በዋናው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ፣ ከባሕር ጠለል 1,177 ሜትር (3,863 ጫማ) ከፍታ፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል በአርባ ምንጭ መንገድ 450 ኪሜ (280 ማይል) ርቀት ላይ ይገኛል።

የዓባያ ሐይቅ ርዝመቱ 81 ኪሜ (50 ማይል)፣ ስፋቱ ደግም 30 ኪሜ (17 ማይል) ሲሆን፣ የሐይቁ አጠቃላይ ስፋት እስከ 1,160ኪሜ² (448 ማይል²) ይደርሳል። የሐይቁ ከፍተኛ ጥልቀት 13 ሜትር (43 ጫማ) ሲሆን፣ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ጥልቀት 7 ሜትር (23 ጫማ ) ነው። የዓባያ ሐይቅ 8 ቢሊዮን ሜትር³ (283 ቢሊዮን ጫማ³) የሚያክል ውኃ እንደሚይዝ ይገመታል።
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   6°17'25"N   37°49'44"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ13 ዓመታት በፊት