አብያታ ሐይቅ

Ethiopia / Oromia / Negele /
 ሐይቅ, caldera (en)

የአብያታ ሐይቅ፣ በአብያታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ፣ በዋናው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ፣ ከባሕር ጠለል 1,581 ሜትር (5,186 ጫማ) ከፍታ ላይ፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል፣ በሞያሌ መንገድ 200 ኪሎ ሜትር (124 ማይል) ርቀት ላይ ይገኛል።

የሐይቁ ርዝመት 14ኪሜ (9 ማይል)፣ ስፋት 11ኪሜ (7 ማይል)፣ አጠቃላይ ስፋት (የቆዳ ስፋት) 205 ኪሜ² (79 ማይል²) ይደርስ እንደነበር ቢታወቅም፣ አሁን ግን፣ ያለአግባብ የሰው ልጅ በሚያደርጋቸው ተግባራት ምክኒያት፣ ሐይቁ በከፍተኛ ደረጃ እየሟሸሸ ነው። በአንድ በኩል በሐይቁ አካባቢ ለዘመናት ተጠብቀው የነበሩት እጅግ በጣም ብዛት የነበራቸው የግራር ዛፎች ተጨፍጭፈው ለከሰል ሽያጭ መዋላቸው ሳያንስ፣ ዛሬ ደግም፣ ከሐይቆቹ ውስጥ የሶዳ አመድ ለማምረት ተብሎ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከጥቅሙ ይልቅ፣ ጉዳቱ ይብሳል። ደን በተደመሰሰ ቁጥር፣ የዝናብ መጥፋትንና የወቅቶችንም መዛነፍ ያስከትላል የሚለው አባባል፣ ተራ ትረካ ሳይሆን በመረጃ የተደገፈ ሐቅ ነው። የዝናብ መጥፋት ሐይቅን ያደርቃል። የአብያታ ሐይቅ መድረቅ ደግሞ፣ በአብያታ ሐይቅ ብቻ አያበቃም፤ የሚያስከተለውም መዘዝ የከፋ ይሆናል። ይህም ከመሆኑ በፊት፣ የአብያታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክን ወደነበረበት ሁኔታ ለመመለስ ሳይዘገይ አስፈላጊ የሆኑትን እርምጃዎች በፍጥነት መውሰድ የውዴታ ግዴታ ሆኖ መታየት ይኖርበታል።
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   7°36'30"N   38°35'29"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ13 ዓመታት በፊት