የመቅደላ አምባ
Ethiopia /
Amhara /
Dese /
World
/ Ethiopia
/ Amhara
/ Dese
ተራራ, ታሪካዊ
የመቅደላ አምባ ደቡብ ወሎ ውስጥ፣ ተንታ ወረዳ፣ ከተንታ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ በኩል የሚገኝ ታሪካዊ ቦታ ነው። በቀድሞው ወቅት የተለየ ሁኔታ የነበረው ሊሆን ቢችልም፣ ዛሬ ግን የመቅደላ አምባ የሚገኘው በመቅደላ ወረዳ ውስጥ ሳይሆን፣ በተንታ ወረዳ ውስጥ ስለሆነና ሁኔታውም ግር ሊል ስለሚችል፣ የሁለቱን ልዩነት በቅድሚያ መገንዘብ ይረዳ ይሆናል።
የአምባው ከፍታ ከባሕር ጠለል እስከ 2,798ሜ (9,180ጫ) የሚደርስ ሲሆን፣ እኢአ በ1860ዓም (እ አ አ 1868 ዓም) በአፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት እና በራበርት ናፒር ይመራ በነበረው በእንግሊዝ ጦር መኃከል በተደረገው ጦርነት፣ በተለያዩ ውስጣዊ በሆኑ ችግሮች ምክኒያት ተዳክሞ የነበረው የንጉሡ ጦር ለሽንፈት ሊጋለጥ ቻለ። ንጉሡም ከጠላት እጅ በመውደቅ ሊከሰት የሚችለውን መዘዝ ለመገንዘብ ጊዜ አልፈጀባቸውም ነበር። ለጠላት እጃቸውን በመስጠት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚዘልቅ ሀፍረትን ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ከማውረስ ይልቅ፣ በቆራጥነት የራሳቸውን ሕይወት በገዛ እጃቸው ለመውሰድ ወሰኑ። ለመጨረሻም ጊዜ የሽጉጣቸውን ቃታ በመሳብ ዘልዓለማዊ ዕረፍትን የተጎናጸፉበት ቦታ ከዚህ ታሪካዊ እና ገናና ከሆነው ከመቅደላ አምባ ላይ ነበር።
ይህን ታሪካዊ ቦታ በአካል ተገኝተው ለመቃኘት ለሚሹ፣ ለአካባቢው ቅርበት ያለው ትልቅ ከተማ ደሴ ነው። ከደሴ ወደ አምባው ለመድረስ ደግሞ ሁለት አማራጭ መንገዶች አሉት። ከሁለቱ አማራጭ መንገደች ደግሞ፣ በሳተላይት ዕይታዎች ላይ በመመርኮዝ፣ ጥሩ ሆኖ የሚታየው ከደሴ ወደ አቀስታ በሚወስደው መንገድ አድርጎ ወደ ተንታ ከታማ የሚያመራውን መምረጥ የተሻለ ይመስላል። በዚህ አቅጣጫ ከደሴ ወደ ተንታ ከተማ የሚወስደው መንገድ አብዛኛውን በአስፓልት የተሠራ ነው፤ ሆኖም ግን ከሁለተኛው አማራጭ የበለጠ ርቀትን ለመሸፈን የግድ ይላል።
ሁለተኛው አማራጭ ከደሴ ወደ ተንታ ከተማ በኩታበር ከተማ አድርጎ የሚወስደው መንገድ ነው። ይህ መንገድ ከመጀመሪያው ምርጫ በ31ኪሜ (19ማይል) እጥረት ቢኖረውም፣ የመንገዱ ሁኔታ አስተማማኝ ካለመሆኑም በላይ፣ በአብዛኛው ጥርጊያ መንገድና ድልድይ አልባ የሆኑ ወቅታዊ ወንዞችን መሻገር ይጠይቃል። በተለይም ወቅቱ የዝናብ ወቅት ከሆነ አደገኛ ሊሆን ስለሚችል ልምድ ያለው ሰው ካልሆነ በስተቀር በዚህ በኩል ላለመጓዝ መወሰን ጥሩ ምርጫ ሳይሆን አይቀርም።
ከደሴ በአቀስታ መንገድ አድርጎ ከዚያም በአጅባር ወደ ተንታ ከተማ ድረስ 135ኪሜ (84 ማይል)የሚያክል ርቀት አለው። ከተንታ ከተማ እስከ መቅደላ አምባ በተለይም፣ የአፄ ቴውድሮስ ሰባስታፖል አለ ወደሚባልበት፣ ሰላምጌ ተብሎ ወደሚጠራው ሰፈር ለመድረስ 17ኪሜ (10.6ማ) ርቀት ያለውን ጥርጊያ መንገድ መጓዝ ይጠይቃል። ከደሴ በኩታበር ከተማ አ ድርጎ ወደ ተንታ ከተማ ለመድረስ 104ኪሜ (65ማ) ያህል ርቀት አለው።

ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥ 11°20'48"N 39°10'55"E
- ግሸን ደብረ ከርቤ 27 ኪሜ
- ላሊበላ 79 ኪሜ
- ድንጋይ ደበሎ ማርያም ቤተክርስቲያን 184 ኪሜ
- ደብረ ብርሃን ሥላሴ 233 ኪሜ
- የአፄ ፋሲል ግቢ 234 ኪሜ
- ደብረ ፀሐይ ቁስቋም ግቢ 236 ኪሜ
- ጎንደር 239 ኪሜ
- አክሱም 315 ኪሜ
- ይሐ 328 ኪሜ
- ደብረ ዳሞ ገዳሞ 337 ኪሜ
- ታጠቅ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት 8 ኪሜ
- ላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ 73 ኪሜ
- ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን 85 ኪሜ
- አቡነ ዮሴፍ ተራራ 90 ኪሜ
- መካነ ኢየሱስ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት 126 ኪሜ
- መካነ ኢየሱስ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት 126 ኪሜ
- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 136 ኪሜ
- ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን 138 ኪሜ
- ዓፄ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት 139 ኪሜ
- ደብረ ታቦር ሆስፒታል 139 ኪሜ