ግሸን ደብረ ከርቤ

Ethiopia / Amhara / Weldiya /
 ተራራ, ታሪካዊ, ገዳም
 ምስል ይጫኑ

ግሸን ደብረ ከርቤ በደቡብ ወሎ፣ አምባሰል ወረዳ ውስጥ፣ በተፈጥሮ የመስቀል ቅርጽን ከያዘው ከግሸን አምባ ላይ የተመሠረተ ገዳም ነው። ይህ ገዳም ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ጥንታዊ ገዳማት ውስጥ አንዱ ነው። ግሸን ደብረ ከርቤን ከሌሎች ገዳማት መኃከል ለየት የሚያደርገው ነገር፣ የመልክዓ ምድሩ ተፈጥሯዊ ቅርጽ ለየት ያለ በመሆኑ ብቻ አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት መስቀል፣ የቀኝ እጁ ያረፈበት "ግማደ መስቀል" ከዚህ ገዳም ውስጥ እንደሚገኝ በምእመናን ዘንድ በከፍኛ ደረጃ የሚታመንበት ነገር ነው። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሚገኙት መረጃዎች መሠረት፣ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ በ፩፬፻፵፮ (1446) ዓመተ ምሕረት ግማደ መስቀሉን ከሌሎች ተጨማሪ ነገሮች ጋር ከስናር (ሱዳን) ወደ ኢትዮጵያ አምጥተው፣ ግሸን አምባ ላይ፣ ከእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ስር በተዘጋጀ ልዩ ቦታ እንዲቀመጥ በማድረጋቸውና፣ እስከዛሬም ድረስ ከዚህ ልዩ ቦታ እንደሚኖር ስለሚታመንበት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምእመናን በየወቅቱ ወደዚህ ክቡር ቦታ እየተጓዙ ጸሎታቸውን ያደርሳሉ። ግሸን አምባ ከባሕር ጠለል 3,019ሜትር (9,905 ጫማ) ከፍታ ላይ የሚገኝ፣ በአምባው ላይ 37.74 ሄክተር (93.27 ኤክረስ) ስፋት ባለው ቦታ ላይ አራት አብያተ ክርስቲያናት ማለትም፣ ቅድስት ማርያም (ግሸን ማርያም)፣ እግዚአብሔር አብ (በመስቀል ቅርጽ የታነጸው)፣ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሚካኤል ይገኛሉ። ግሸን ደብረ ከርቤ በተለያዩ ወቅቶች የተላያዩ መጠሪያ ስሞች እንደነበፘት መረጃዎች ይገልፃሉ፥ ግሸን ማርያም፣ ደብረ ነጎድጓድ፣ ደብረ ነገሥት፣ ደብረ ከርቤ።
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   11°31'12"N   39°21'31"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ11 ዓመታት በፊት