ሰይጣን መጣያ

Ethiopia / Amhara / Addi Arkay /
 ምስል ይጫኑ

ሰይጣን መጣያ የሰሜን ተራራዎች አካል ሲሆን፣ የተራራው ስም አሰጣጥ
ከተራራው ግዙፍነት (ከፍታ) ጋር የተያያዘ ነው። የተራራውን ግዙፍነት
ከቅርብ ሆኖ ለተገነዘበ ሰው፣ የአካባው ነዋሪዎች ለምን የዚህ ዓይነት
ስም እንደሰጡት ለመረዳት አዳጋች አይሆንም። ከሰይጣን መጣያ
ስር፣ በማይፀምሪ ከተማ በኩል አዲ ወሰኒ የምትባል ሰፈር ትገኛለች።
በሰሜን ተራራዎች አካባቢ የሚገኙ ብዙ አስደናቂ(አስገራሚ) የቦታ
መጠሪያ ስሞች አሉ፤ ከነዚህም ውስጥ፣ ቡሃይት፣ መቃብር አምበሳ፣
ጭንፍራ የሚባሉትን መጥቀስ ይቻላል። ጭንፍራ ተራራ ሲሆን፣
ጭንፍራ የሚለው ስም የተሰጠው፣ ተራራውን ለመውጣት ካለው
አዳጋችነት የተነሳ ተራራውን ለሚወጣ ሰው በጉዞው ወቅት
ጭኑ እንዳይላላጥ ለማስጠንቀቅ ተብሎ ጭንፍራ (ጭንህን ፍራ)
የሚል ስም ተሰጠው ይባላል። (ምንጭ፦ በአካባቢው ነዋሪዎች
የሚነገር አፈታሪክ)
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   13°28'2"N   38°14'38"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ15 ዓመታት በፊት