ደንዲ ሐይቅ

Ethiopia / Oromia / Hagere Hiywet /
 crater lake (en)  ምድብ ይጨምሩ
 ምስል ይጫኑ

ደንዲ ሐይቅ በምዕራብ ሸዋ፣ ከአዲስ አበባ 127ኪሜ (79 ማይል) ርቀት፣ ከባሕር ጠለል 2,836 ሜትር (9,305 ጫማ) ከፍታ ላይ የሚገኝ፣ በእሳተገሞራ ፍንዳታ ምክኒያት የተፈጠረ ልዩ፣ ድንቅ እና ውብ የሆነ ቅርፅ ያለው ሐይቅ ነው።

ይህ፣ የ5ኪሜ (3 ማይል) ርዝመት እና እስከ 2ኪሜ (1.2 ማይል) የሚደርስ ስፋት ያለው ሐይቅ፣ በሚገርም ሁኔታ፣ በእስተገሞራው ፍንዳታ በተፈጠረው ክስተት ምክኒያት፣ ከወገቡ ላይ በጣም ጠባብ የሆነ፣ የ220ሜትር (722 ጫማ) ብቻ የሚያክል ስፋት ያለው ሲሆን፣ ይህ ክፍት ቦታ ባይፈጠር ኖሮ፣ ደንዲ አንድ ብቻ ሳይን፣ ሁለት፣ የተከፋፈሉ ሐይቆች ሊሆን ይችል እንደነበር መገመት ይቻላል። የደንዲ ሐይቅ ቆዳ ስፋት 8ኪሜ² (3ማ²) እንደሚሆን ይገመታል።

ከሐይቁ በስተሰሜን ማዕከላዊ ዳርቻ ላይ፣ የዳግማዊ ምኒልክ ታማኝ የጦር አዛዥ በነበሩት፣ በፍታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ እንደተገነባ የሚነገርለት ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና የፍታውራሪው ቤት ይገኛሉ።
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   8°50'30"N   38°0'40"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ11 ዓመታት በፊት