አዲስ አበባ ፊስቹላ ሆስፒታል (አዲስ አበባ)

Ethiopia / Addis Abeba / አዲስ አበባ
 ሆስፒታል  ምድብ ይጨምሩ
 ምስል ይጫኑ

በአውሮፓ አቆጣጠር 1974 ዓመተ ምሕረት፣ ዶክተር ካትሪን ኃምሊን እና አሁን በሕይወት ከተለዩአቸው ከባለቤታቸው፣ ረጂናልድ ኃምሊን ጋር በመተባበር፣ አዲስ አበባ የሚገኘውን የፊስቹላ ሆስፒታል መሠረቱ። ሆስፒታሉ፣ በወሊድ ምክኒያት ሴቶች ላይ የሚደርሰውን (በሕክምና አጠራር፣ ፊስቹላ ተብሎ የሚጠራውን) የአካል ጉዳት፣ በቀዶ ጥገና ሕክምና ለመፈወስ ይቻል ዘንድ፣ የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የሆኑትና የተከበሩት፣ ሁለቱ ዶክተሮች የመሠረቱት ማእከል ነው። እነሱም፣ ስለግል ኑሮአቸው ሳይጨነቁ ወይም ደከመን ሳይሉ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት፣ ብዛት ያላቸው እህቶችና እናቶች፣ ከራሳቸው ቁጥጥር ውጭ በሆነና ባላጠፉት ነገር፣ ከሕብረተሰብ ብቻ ሳይሆን፣ ከራሳቸው ቤተሰብ ሳይቀር ተገልለውና አንገታቸውን ደፍተው እንዲኖሩ ከተገደዱበት፣ ከሀዘንና የጭለማ ኑሮ ተላቀው፣ ዛሬ ምሥጋናቸውን ለዶክተሮቹ እያቀረቡ፣ አንገታቸውን ቀና አድርገው፣ ቆንጆውን ፈገግታቸውን ለማሳየት በቅተዋል። ምሥጋና ይድረሳቸውና፣ ለኃምሊን ቤተሰብ።

ከአዲስ አበባው በተጨማሪ፣ በባሕር ዳር፣ ሐረር፣ መቀሌ፣ መቱ እና ይርጋ ዓለም ተጨማሪ የፊስቹላ ሕክምና ማእከሎች ተከፍተዋል።
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   9°0'19"N   38°42'53"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ9 ዓመታት በፊት