አጆራ ፏፏቴ

Ethiopia / Southern / Areka /
 ምስል ይጫኑ

አጆራ ፏፏቴ በመባል የሚታወቁት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሶዶ ከተማ ሰሜናዊ ምዕራብ በኩል የሚገኙት መንቲያ ፏፏቴዎች ናቸው። ፏፏቴዎቹም ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ ከሚወስደው አውራ ጎዳና በስተምዕራብ በኩል፣ በግምት 16ኪሜ (10 ማይል) ላይ ይገኛሉ። ከዋናው መንገድ ተገንጥሎ ወደ ፏፏቴዎቹ የሚውስደው ጥርጊያ መንገድ፣ ከሶዶ በስተሰሜን 28ኪሜ (17.4 ማይል) ርቃ ከምትገኘው አረካ ከምትባል ትንሽ ከተማ አለፍ ብሎ 7ኪሜ (4 ማይል) ርቀት ላይ ይገኛል። ሁለቱ ፏፏቴዎች የተመሰረቱት ሶኬ እና አጀቾ ተብለው በሚጥሩ ትናንሽ ወንዞች ሲሆን፣ ሶኬ ወንዝ በሰሜን፣ አጀቾ ደግሞ በስተደቡብ በኩል የሚገኘው ነው። በሁለቱ ፏፏቴዎች መሀከል ያለው ርቀት በቀጥታ መስመር ሲለካ 650 ሜትር (2,133 ጫማ) እንደሚሆን ይገመታል። ወንዞቹም ከፏፏቴዎቹ አለፍ ብለው ውሕደት ይፈጥሩና፣ ለተጨማሪ 10ኪሜ (6 ማይል) ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በማምራት፣ ከአበይት የኢትዮጵያ ወንዞች ውስጥ አንዱ ከሆነው ከኦሞ (ጊቤ) ይቀላቀላሉ። ከጎብኚዎች በተደጋጋሚ የተሰነዘሩ ማሳሰቢያዎች፣ ለዕይታ አመቺ የሆኑት ቦታዎች የሚያዳልጡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ሲሆን፣ ለአካባቢውም ባዕድ የሆኑ ነገሮችን፣ ማለትም እንደ ፕላስቲክ ጠርሙስ እና የመሳሰሉትን ከመጣል እንዲቆጠቡ ነው።
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥   7°10'36"N   37°36'1"E
ይህ ዓምድ የመጨረሻው ዕርማት የተደረገበት ከ12 ዓመታት በፊት