ጣና ሐይቅ
Ethiopia /
Amhara /
Werota /
World
/ Ethiopia
/ Amhara
/ Werota
/ ኢትዮጵያ / /
ሐይቅ
ምድብ ይጨምሩ
ጣና ሐይቅ የዓባይ ወይም ደግሞ፣ በዓለም ዙሪያ ብሉ ናይል በመባል የሚታወቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ወንዝ መነሻ ነው። በተጨማሪም፣ ጣና ሐይቅ በቆዳ ስፋት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሐይቆች ሁሉ የሚበልጥ አብይ ሐይቅ ነው። ሐይቁ በምዕራብ ጎጃም ውስጥ፣ ከባሕር ጠለል በ1,788 ሜትር (5,866 ጫማ) ከፍታ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ሰሜናዊ ምዕራብ በኩል፣ በጎጃም መንገድ 555 ኪሜ (345 ማይል) ርቀት ላይ ይገኛል። በሐይቁ ውስጥ ብዛት ያላቸው ደሴቶች አሉ። ከዴሴቶቹም መሃከል በአብዛኛዎቹ ላይ፣ በሀገሪቱ ውስጥ በጥንታዊነታቸው የሚታወቁ በዛ ያሉ ገዳማት ይገኙባቸዋል።
ጣና ሐይቅ 79 ኪሜ (49 ማይል) ፣ በ 64 ኪሜ (40 ማይል) የሚደርስ ስፋት አለው። የሐይቁ ጥልቀት ሲለካ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ጥልቀት 9 ሜትር (30 ጫማ) ሲሆን፣ ከፍተኛው ጥልቀት 14 ሜትር (46 ጫማ) ይደርሳል። የሐይቁ አጠቃላይ ስፋት 3,200 ኪሜ² (1,236 ማይል²) ሲሆን፣ እስከ 28 ቢሊዮን ሜትር³ (988.8 ቢሊዮን ጫማ³) የሚሆን ውኃ ሊይዝ እንደሚችል ይገመታል። ስለሆነም፣ በውኃ ይዘት መጠን (ቫልዩም) አንፃር ሲታይ፣ የጣና ሐይቅ፣ ከሻላ ሐይቅ ቀጥሎ፣ በሀገሪቱ ውስጥ የሁለተኛ ቦታን ይይዛል።
ጣና ሐይቅ ብዛት ያላቸው መጋቢ ወንዞች ያሉት ቢሆንም፣ ከወንዞቹ መሃከል መጠኑ ትልቅ የሆነው የግልገል ዓባይ ወንዝ ነው። በዚህም ምክኒያት፣ ከጣና ሐይቅ በስተደቡብ 200 ኪሜ (124 ማይል) ርቀት ላይ፣ ከግሽ ዓባይ የሚፈልቀው ግልገል ዓባይ፣ የዋንኛው የዓባይ ወንዝ ትክክለኛ ምንጭ እንደሆነ በሰፊው ይታመናል።
የዓባይ ወንዝ መውጫው በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ በኩል ሲሆን፣ ወንዙ በሐይቁ ዳር ላይ የተመሰረተች፣ ዘመናዊ የሆነችውን የባሕር ዳር ከተማ በማቋረጥ ረዥሙን ጉዞ የሚጀምረው ከዚህ ነው።

ዊኪፒዲያ ዓምድ: http://am.wikipedia.org/wiki/ጣና_ሐይቅ
ቀረብ ያሉ ከተማዎች:
መጋጠሚያ፥ 11°57'5"N 37°18'29"E
- አንገረብ ውኃ ማጠራቀሚያ ግድብ 77 ኪሜ
- አድዋ ሰውሰራሽ ሐይቅ 306 ኪሜ
- ደቅ ደሴት 5.7 ኪሜ
- ብርጊዳ ማርያም ገዳም 29 ኪሜ
- መድኃኒ ዓለም ገዳም 29 ኪሜ
- ጎርጎራ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት 33 ኪሜ
- መትራሐ ደሴት 38 ኪሜ
- ጎንደር አፄ ቴድሮስ ኤርፖርት 65 ኪሜ
- ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን 67 ኪሜ
- አዘዞ የመብራት ኃይል ንኡስ ጣቢያ 68 ኪሜ
- አዘዞ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት 68 ኪሜ
- አፄ ፋሲል ትምሕርት ቤት 68 ኪሜ